ሄፓታይተስ ቢ

2023-11-156 min read
የጉበት በሽታበቫይረስ የተከሰተ የጉበት በሽታ
ሄፓታይተስ ቢ

ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው?

ሄፓታይተስ ቢ በዓለም ላይ በብዛት ጉበትን ከጥቅም ውጭ የሚያደርግ ነው፡፡ የሚመጣውም ሄፓታይተስ ቢ (HBV) በሚባል ቫይረስ ሲሆን ቫይረሱ ጉበትን በማጥቃት ጉዳት ያደርሳል፡፡ የሚተላለፈው በደም፣ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ መርፌዎችን በመጋራት ወይም ድጋሚ በመጠቀም እንዲሁም በበሽታው ከተያዘች እናት ወደ ልጅ በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅት ነው፡፡ በርካታ በበሽታው የተያዙ ጎልማሶች ሄፓታይተስ ቢ ን ያለምንም ችግር ከሰውነታቸው እንዲወገድ ማድረግ ችለዋል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጎልማሶች እና በበሽታው በጣም የተጠቁ ህፃናት እና ታዳጊዎች ቫይረሱን ከሰውነታቸው ማስወጣት አለመቻላቸውን ተከትሎ በፀና ህመም ውስጥ ገብተዋል፡፡ መልካሙ ዜና ሄፓታይተስ ቢ ን ለመከላከል አስተማማኝ ክትባት መኖሩ ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ቀድሞውኑ በሄፓታይተስ ቢ ለተጠቁት በአዲስ መልኩ ህክምና መደረጉ ነው፡፡

በሄፓታይተስ ቢ የተጠቁት ሰዎች ምን ያህል ናቸው?

በመላው ዓለም 2 ቢሊየን ሰዎች (ከ3 ሰዎች መካከል1) በሄፓታይተስ ቢ የተጠቁ ሲሆን 257 ሚሊየን የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ በፀና የታመሙ ናቸው፡፡ (ይህም ማለት ቫይረሱን ከሰውነታቸው ማስወገድ አይቻልም) በሄፓታይተስና ከእሱ ጋር በተያያዘ 700,000 የሚጠጉ ሰዎች በየዓመቱ ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡

ሄፓታይተስ ቢ በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች ለምን በብዛት ይከሰታል?

ሄፓታይተስ ቢ የእድሜ እና የብሄር ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም ሰው ሊይዝ ይችላል፤ ነገር ግን ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚከሰትባቸው ከተወሰኑ የዓለም ክፍሎች ያሉ ሰዎች ማለትም እንደ ኤሲያ፣ የአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ በበሽታው የመያዝ እድላቸው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡ በነዚህ ቦታዎች በተወለዱ አሜሪካውያን (ወይም ቤተሰቦቻቸው በተወለዱት) ላይ ሄፓታይተስ ቢ በብዛት ይከሰታል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ በተወሰኑ የኣለማችን ክፍሎች ላይ በብዛት የተለመደ ሲሆን፤ ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት የሚጠቀሰው በቦታዎቹ ላይ ቀደም ብለው በሄፓታይተስ ቢ የተጠቁ ብዙ ሰዎች መኖራቸው ነው፡፡ ምንም እንኳን ሄፓታይተስ ቢ "የኤስያውን በሽታ" ወይም "የአፍሪካውያን በሽታ" ባይሆንም ከነዚህ ቦታዎች በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የበከለ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን ወደሌሎች እንዲተላለፍ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስጋቱ በጨመረ ቁጥር በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ በቫይረሱ የተያዙ ምዕራባውያን ቁጥር ማነሱን ተከትሎ፣ ይህ ቡድንያለው የመያዝ እድሉ ዝቅ ያለ ነው፡፡ ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚታይባቸው አካባቢዎች ያሉ ሰዎች በብዛት የሚያዙት በወሊድ ጊዜ ማለትም እናቶች ሲወልዱ ባለማወቅ ቫይረሱ ወደ ልጃቸው ይተላለፋል፡፡ ታዳጊ ህፃናት የሚኖሩት ቫይረሱ ካለበት የቤተሰቡ አባል ጋር በየቀኑ የቀረበ ግንኙነት የሚደርጉ ከሆነ የመያዝ እድል አላቸው፡፡ ህፃናትና ታዳጊዎች በሄፓታይተስ ቢ ከሌሎች በበለጠ በከፍተኛ ደረጃ ይጠቃሉ፤ ለዚህም ምክንያቱ ብዙም ያልጠነከረው በሽታን የመከላከል አቅማቸው ቫይረሱን ለማስወገድ ስለሚቸገር ነው፡፡

ስለ ሄፓታይተስ ቢ ለምንድን ነው ትኩረት መስጠት ያለብኝ?

ስር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የከፋ የጉበት ህመምን ማለትም እንደ ሰርሆሲስ ወይም የጉበት ካንሰርን ያስከትላል፡፡ ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ቀድሞ ምርመራ ማድረግ ቀድሞ ህክምና ለማግኘትና የግለሰቡንም ህይወት ለማዳን ያግዛል፡፡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌሎች ያስተላልፋሉ፡፡ በርካቶች አለመያዛቸውን ባለማወቃቸው የተነሳ፣ ሳያውቁ ቫይረሱን ወደ ብዙ ሰዎች ያስተላልፋሉ፡፡ ሰዎች ምርመራ ካላደረጉ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ሄፓታይተስ ቢ ወደ ተለያየ ትውልድ ብሎም ማህበረሰብ የሚተላለፍ ነው፡፡ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ትውልዶች መያዛቸውን ተከትሎ ሄፓታይተስ ቢ "በመወለድ የሚመጣ ነው" የሚል አንድ የተለመደ አባባል አለ፡፡ ነገር ግን ሄፓታይተስ ቢ በዘር የሚመጣ በሽታ አይደለም፣ ሄፓታይተስ ቢ የሚመጣው በቫይረስ፣ እንዲሁም በብዛት በቤተሰብ አባላት መካከል ከእናት ወደ ልጅ ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ በተፈጠረ የደም ንክኪ ነው፡፡ ቤተሰቦች በሄፓታይተስ ቢ የመያያ ኡደትን በመመርመር፣ ክትባት በመከተብ እና ህክምና በመከታተል ማስቆም ይችላሉ፡፡

ሄፓታይተስ ቢ ለምንድን ነው እጅግ አደገኛ የሆነው?

ሄፓታይተስ ቢ አደገኛ ነው፤ ምክንያቱም "ዝምተኛው በካይ" በመሆኑ ሰዎች ምንም ነገር ሳያውቁ ስለሚይዛቸው ነው፡፡ በሄፓታተስ ቢ የተያዙ በርካታ ሰዎች ስለመያዛቸው አለማወቃቸውን ተከትሎ ቫይረሱንበደማቸው እና በሌሎች በተበከሉ የሰውነታቸው ፈሳሾች ወደ ሌሎች ያዛምታሉ፡፡ በፀና የታመሙት ጉበታቸው ስራ የማቆም ስጋት እንዲሁም በስተመጨረሻም ሲርሆሲስ ወይም የጉበት ካንሰር የመከሰታቸው እድል ይጨምራል፡፡ ቫይረሱ ለብዙ ዓመታት ድምፁን አጥፍቶ ሳይለይ ከቆየ በጊዜ ሂደት በተከታታይ ዓመታት በጉበት ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ያለ ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው?

የበመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለ ሄፓታይተስ ቢ እስከ ስድስት ወር (በምልክት ወይም ያለ ምልክት) ድረስ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ሲሆን በዚሁ ጊዜም የተያዘው ግለሰብ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ማስተላለፍ ይችላል፡፡ በጅማሮ ደረጃ ላይ ያለ ሄፓታይተስ ቢ ምልክቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ የመገጣጠሚያ እና ጡንቻ ህመም፣ ዝቅተኛ መጠን ያለው ትኩሳት እና የጨጓራ ህመምም ሊኖር ይችላል፡፡ ምንም እንኳን በርካታ ሰዎች ላይ ምልክቱ ባይታይም፣ በቫይረሱ ከተያዙ ከ60-150 ቀናት በኋላ ቫይረሱ ሊገኝባቸው የሚችል ሲሆን፤ ይህም በአማካይ 3 ወር ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጠንከር ያሉ ምልክቶች የሚታይባቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ንፍጥ፣ ማስመለስ፣ ጃውንዳይስ (የዓይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን) አሊያም የጨጓራ መነፋት ሲሆኑ፣ ወደ ጤና ባለሙያ እንዲሄዱ ምክንያት ይሆናል፡፡ ቀላል የሚባል የደም ምርመራ ለአንድ ግለሰብ በደም ውስጥ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ስለመኖሩ ሊነግረው ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ላለ ሄፓታይተስ ቢ ምርመራ አድርገው ከሆነ ከ6 ወራት በኋላ ዶክተሩ በድጋሚ ደሞትን በመመርመር እንደተሻለዎት አሊያም ሄፓታይተስ ቢ እንደፀናብዎት ማረጋገጥ አለበት፡፡ የጤና ድጋፍ ባለሙያው በደሞት ውስጥ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ አለመኖሩን እስኪያረጋግጥልዎት ድረስ ወደሌሎች ላለማስተላለፍ ጥረት ማድረግ አለብዎት፡፡ የወሲብ አጋርዎ (አጋርዎችዎ) እና የቤተሰብ አባላት (በአንድ ቤት ውስጥ በጋራ የምትኖሩ) የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ምናልባትም በቫይረሱ ያልተያዙ ከሆኑ እና የሄፓታይተስ ቢ ን ክትባት ያልወሰዱ ከሆኑ ክትባቱን በተከታታይ መውሰድ አለባቸው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሄፓታይተስ ቢ ላለባቸው ሰዎች የሚሰጥ የሄፓታይተስ ቢ ህክምና የለም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን ሄፓታይተስ ቢ ለማስወገድ የሚደረግ ህክምና ስለሌለ የተያዙ ጎልማሶች በራሳቸው ጊዜ ይሻላቸዋል፡፡ አንዳንዴ ምልክቶቹ በፀና የሚታይበት ህመምተኛ ለአጠቃላይ ድጋፍ ሲባል ህክምና ሊደረግለት ይችላል፡፡ እረፍት እንዲያገኙ ማድረግ እና ምልክቶቹን መቆጣጠር የዚህ ህክምና ቀዳሚ ግቦች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ የሚከሰት፣ ህይወትን አደጋ ውስጥ የሚከተው “ፉልሚናንት ሄፓታይተስ”በመጀመሪያ ደረጃ የቫይረሱ መያዝ ወቅት ሊከሰት የሚችል ሲሆን፤ ይህም ግለሰቡን ለድንገተኛ የጉበት ስራ ማቆም ሊዳርገው ስለሚችል ወዲያውኑ በፍጥነት ፈጣን የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ መደረግ አለበት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ላለ የሄፓታይተስ ቢ ምልክቶች ጠቃሚ ከሆኑት ምክሮች መካከል አልኮልን አለመጠቀም፣ ሲጋራን አለማጨስ ወይም መቀነስ፣ ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ፣ ከጤና ባለሙያ ጋር በሚወስዷቸው ማናቸውም መድሀኒቶች ዙሪያ መመካከር (በትዕዛዞች፣ በመድሀኒት አወሳሰድ፣ በሚወስዷቸው ቫይታሚኖችና ሌሎች የባህል መድሀኒቶች ዙሪያ)፡፡ ይህ ያሏችሁን ማናቸውንም ሌሎች ጥያቄዎች ለመጠየቅ ጥሩ ጊዜ ነው፡፡ ቫይታሚኖችን እና በምግብ መልክ የሚወሰዱ መድሀኒቶች መጠቀም እንዳይድኑ ከማድረግ ይልቅ በጉበት ላይ የበለጠ ጉዳት እንዲደርስ ያደርጋሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ካለ የቫይረሱ መያዝ ለመዳን በህክምና ባለሙያ የሚደረግልዎትን ማንኛውንም አይነት የደም ምርመራ በአግባቡ መከታተል አለብዎት፡፡

ስር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው?

ከስድስት ወር በኋላ (ከመጀመሪያው የደም ምርመራ ውጤት በኋላ) የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ እንዳለባቸው ያወቁ ሰዎች በሽታው ስር ስለመስደዱ ለማረጋገጥ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህም ማለት የሰውነታቸው በሽታን የመከላከል አቅም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን ለማስወገድ ባለመቻሉ በሰውነታቸው በደምና በጉበት ውስጥ እንዲቆይ ይሆናል፡፡ ስር የሰደደን ህመም ለማከምና ለማገዝ የሚደረግ ውጤታማ አሰራር ቢኖርም በሽታውን ግን ማዳን አይቻልም፡፡ በሽታው ስር ከሰደደ በቀሪው የህይወት ዘመንዎ ከቫይረሱ ጋር አብረው ይኖራሉ፡፡ ስር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ያለባቸው ሰዎች ባለማወቅ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ያስተላልፋሉ፡፡ ስር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ወደ ጠነከረ የጉበት ህመም ማለትም ወደ ሰርሆሲስ ወይም የጉበት ካንሰር ያመራል፡፡ በፀና የታመመ ሰው ሁሉ የጠነከረ የጉበት ህመም ይይዘዋል ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በበሽታው ምንም ካልተያዘው ሰው በበለጠ የመያዝ እድል አለው፡፡ ስር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የመፈጠር እድሉ ግለሰቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቫይረሱ በተጋለጠበት እድሜ ይወሰናል፡፡ 90% በሚሆኑትና በቫይረሱ በሚያዙት አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት እና ልጆች ላይ ሄፓታይተስ ቢ ስር ይሰዳል፡፡ እስከ 50% የሚደርሱትና በቫይረሱ የተያዙ ህፃናት (ከ1-5 ዓመት) ስር ለሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ይዳረጋሉ፡፡ 5-10% የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙ ጎልማሶች ስር ለሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ይጋለጣሉ (ከነዛ ውስጥ 90% ያገግማሉ) ስር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ እንዳለ ማወቅ በእጅጉ የሚረብሽ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቹ ሰዎች ምልክቶቹ ባለመታየታቸው ለሄፓታይተስ ቢ ምርመራ የሚያደርጉት በቫይረሱ ከተያዙ ከአስርት አመታት በኋላ በመሆኑ ስር ለሰደደው የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ የሚያስደነግጥና የሚያስገርም ሊሆን ይችላል፡፡ መልካም የሚባለው ዜና አብዛኞቹ ስር ከሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ጋር ያሉ ሰዎች ረዥምና ጤናማ ኑሮ እንደሚኖሩ መጠበቅ አለባቸው፡፡ በቫይረሱ የተያዘች ነፍሰ ጡር እናት በወሊድ ወቅት አዲስ ወደተወለደው ልጅዋ ቫይረሱን ልታስተላልፍ ትችላለች፡፡ ስለሆነም አዲስ የሚወለዱት ጨቅላ ህጻናት በወሊድ ወቅት የመያዝ እድላቸው ከፍ ስለሚልና ከተያዙም ስር ስለሚሰድባቸው፣ ዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት እና በአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ሁለቱም ሁሉም ህፃናት እንደተወለዱ በ 12-24 ሰአታት ውስጥ የሄፓታይተስ ቢ ክትባትን መውሰድ እንዳለባቸው በጋራ ይመክራሉ፡፡ ነፍሰ ጡር ከሆኑ እና በቫይረሱ መያዝዎትን ካወቁ የወለዱት ልጅዎ በተወለደ ከ12-24 ባሉት ሰዓታት የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ማግኘት አለበት፡፡ የሄፓታይተስ ቢ በሽታን ማዳን ባይቻልም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን የሚቆጣጠርና በጉበት ላይ ጉዳት እንዳያመጣ የሚስቆም ውጤታማ መድሀኒት አለ፡፡ በጥናት ላይ ያለና ወደፊት በሽታውን ማዳን እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት አዲስ መድሀኒት ወደፊት ይመጣል፡፡ ምንም እንኳን ከባድ የጉበት ህመም ወይም የጉበት ካንሰር የመከሰቱ እድል በቫይረሱ ካልተያዙት በበለጠ ስር በሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ህሙማን ላይ ቢታይም፤ ግለሰቡ ሊተገብራቸው የሚገቡና ችግሩን ለመቀነስ የሚረዱ ቀላል ተግባራት አሉ፡፡ በየስድስት ወሩ (አለበለዚያም በዓመት አንድ ግዜ) የጉበት ስፔሻሊስት ወይም ስለ ሄፓታይተስ ቢ እውቀቱ ወዳለው የጤና ባለሙያ በመሄድ የጉበትዎን ጤንነት ማስመርምር ያስፈልጋል፡፡ ከጤና ባለሙያዎ ጋር ስር ለሰደደው የሄፓታይተስ ቢ የሚደረግልዎት የህክምና ክትትል የከፋ የጉበት ህመም ወይም የጉበት ካንሰር እንዳይከሰት ለመከላከል እንደሚረዳ ተነጋገሩ፡፡ ወደ ጤና ተቋም በሚሄዱበት ጊዜ የጤና ባለሙያው ለጉበት ካንሰር እርስዎን መምረጡን እርግጠኛ መሆንዎ፤ ቫይረሱን ቀድሞ በመለየት የበለጠ ህክምና እንዲያገኙና ህይወትዎ እንዲረዝም ለማድረግ ስለሚረዳ ነው፡፡ በጉበትዎ ላይ በርከት ያሉ መጨናነቆችን ስለሚያስከትሉ አልኮል እና ማጨስን ያስወግዱ አሊያም ይቀንሱ፡፡ ቅባት የበዛባቸው ምግቦች ለጉበት ስለሚከብዱ፣ የበሰሉ አትክልቶችን በመመገብ ጤናማ አመጋገብ ይኑረን፡፡

“በሽታው ስር የሰደደበት” ማለት ምን ማለት ነው?

የሆነ አንድ ግለሰብ በሄፓታይተስ ቢ በፅኑ ከታመመ፣ ዶክተሩ “በፅኑ የታመመ”ብሎ ወደ ሌሎች ይልከዋል፡፡ “በፅኑ የታመመ”ማለት ግለሰቡ ስር ሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ያለበት እና ቫይረሱን ወደሌሎች ማስተላለፍ የሚችል እንደሆነ እንዲሁም በዶክተር ክትትል ሊደረግለት እንደሚገባ ለማመላከት ነው፡፡

ለሄፓታይተስ ቢ ህክምና አለው?

አንዳንድ ጎልማሶች ያለምንም መድሀኒት በመጀመሪያ ደረጃ ካለ የቫይረሱ መያዝ ራሳቸውን ያድናሉ፡፡ ስር በሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ለተያዙ ጎልማሶች፣ ህፃናት እና ጨቅላ ህፃናት ምንም አይነት መድሀኒት የለም፡፡ ነገር ግን መልካም የሚባለው ዜና በፀና በታመመው ህመምተኛ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቫይረሱን በማዳከም የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጉበት ህመም መቀነስ የሚያስችል ህክምና አለ፡፡ የሚራቡት የሄፓታይተስ ቢ ቫይረሶች ቁጥር በቀነሰ ጊዜ በጉበት ላይ የሚደርሰው ጉዳትም ይቀንሳል፡፡ ያሉት ተስፋ ሰጪ ምርምሮች ሲታዩ፣ ወደፊት ስር የሰደደውን ሄፓታይተስ ቢ ለማከም የመረዱ መድሀኒቶች እንደሚገኙ ታላቅ ተስፋ አለ፡፡ የእኛንይጎብኙ መድሀኒት ተመልከት በመሞከር ላይ ያሉ የመድሀኒት ዝርዝሮችን ለማየት፡፡

የእኔን ሄፓታይተስ ቢ ን ለማከም ምን አማራጮች አሉ?

በመጀመሪያ ደረጃ ላለ የቫይረሱ መያዝ እረፍት ከማድረግና ማንኛውንም የበሽታውን ምልክቶች ከመቆጣጠር የዘለለ ምንም አይነት ህክምና የለም፡፡ ስር ለሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የተለያዩ ህክምናዎች አሉ፡፡ በሄፓታይተስ ቢ በፅኑ የታመመ ሰው ሁሉ ህክምና እንደማያስፈልገው መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ህክምና እንደሚስፈልግህ አሊያም ሁኔታውን አየተከታተልክ ለመጠበቅ እንድትወስን ዶክተርህ ያግዝሀል፡፡ የተለያዩ የአንቲቫይራል ህክምናዎች የሄፓታይተስ ቢ ን ቫይረስ ከመባዛት ይገታሉ አሊያም ይቀንሳሉ፤ ይህም በጉበት ላይ የሚደርሰውን የማቃጠል ስሜት እና መሰል ጉዳትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ እነዚህ አንቲቫይራሎች በፒል መልክ በቀን አንድ ጊዜ ቢያንስ ለ 1 ዓመትና ከዚያም በላይ በፒል መልክ ይወሰዳሉ፡፡ በአሜሪካ 6 በኤፍ.ዲ.ኤ እውቅና የተሰጣቸው አንቲቫይራሎች አሉ፤ ነገር ግን ሶስቱ “በመጀመሪያው መስመር ያሉ”የሚባሉት አንቲቫይራሎች ይመከራሉ፦ቴኒፎቪር ዲሶፕሮክሲል (ቪሬድ/ቲ.ዲ.ኤፍ)፣ ቴኖፎቪር አላፍናማይድ (ቬምሊዲ/ቲ.ኤ.ኤፍ) እና ኢንትካቪር (ባራክሉድ)፡፡ መጀመሪያው መስመር ላይ ያሉት አንቲቫይራሎች አስተማማኝና በጣም ውጤታማ በመሆናቸው ይመከራሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያሉት የሚባሉት አንቲቫይራል ህክምናዎች ውጤት ካላመጡ ወይም አንሱን የማግነት እድል ከሌላቸው ሌሎች አማራጮች አሉ፦ telbuvidine (Tyzeka፣ Sebivo)፣ adefovir dipivoxil (Hepsera)፣ እና lamivudine (Epivir-HBV፣ Zeffix፣ Heptodin)፡፡ ምንም እንኳን ኤፍ.ዲ.ኤ እነዚህን አንቲቫይራሎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ቢመክርም ስር የሰደደውን ሄፓታይተስ ቢ ን ሙሉ በሙሉ ማከም አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጉበት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት እና የጉበት ካንሰርን ለመቀነስ ይችላሉ፡፡ አንቲቫይራሎች ዝም ተብለው የሚወሰዱ እና የሚቆሙ ባለመሆናቸው ለሄፓታይተስ ቢ ተብሎ የሚደረገውን ህክምና ከመጀመር በፊት እውቀቱ ያለው ዶክተር ጥልቅ ምርመራ ማድረግ አለበት፡፡ ኢሚዩኖሞዱሌተር መድሀኒቶች የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን በመቆጣጠር የሰውነት የመከላል ብቃትን ከፍ ያደርጋል፡፡ ከ 6 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በመርፌ የሚሰጡ ናቸው፡፡ በብዛት የታዘዘው ኢንተርፌሮን አልፋ-2b (Intron A) እናፔጊሌትድ ኢንተርፌሮን (Pegasys) ናቸው፡፡ እርስዎና ዶክተርዎ ካሉት የህክምና አማራጮች መካከል ለእርስዎ የተሻለውን ለመምረጥ እንዲቻል መነጋገር አለባችሁ፡፡ ለአብዛኞቹሰዎች መድሀኒቶቹ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን ወይ ይቀንሳሉ አሊያም ያስቆማሉ፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ ህመምተኛው የተሻለ ስሜት ይሰማዋል፤ ምክንያቱም ጉበቱ ላይ በቫይረሱ እየደረሰበት የነበረው ጉዳት እየቀነሰ ይመጣል፤ አሊያም ለረዥም ጊዜ ሲወሰድ ድጋሚ ሊያገረሽም ይችላል፡፡